የትራምፕ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረው የኢሚግሬሽን ሕግን ኦባንግ ሜቶና ሳዲቅ አህመድ እንዴት ያዩታል?

የትራምፕ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረው የኢሚግሬሽን ሕግን ኦባንግ ሜቶና ሳዲቅ አህመድ እንዴት ያዩታል?

Published Posted on by | By TZTA News
ሕብር ራድዮ ልዩ ዘገባ <…ዛሬ ዶናልድ ትራምፕ የሚያደርገውን ዘረኛ እርምጃ በአገሪቱ የነጭ የበላይነትን አመጣለሁ ነው የእሱ አሜሪካን ዳግም ታላቅ አደርጋለሁ የሚለው ይህን መሰሉን ዘረና እርምጃ ጭምር ነው አዲስ አይደለም በምርቻ ቅስቀሳ ወቅት የተናገረውን ነው ያደረገው …እኛ በያለንበት መተባበር ከሌሎች ጋር በጋራ ድምጻችንን ማሰማት አለብን። ዛሬ ከኤርፖርት ይመለሱ የተባሉት በሁለተናው የኣለም ጦርነት ወደ አሜሪካ ሊገቡ ሲሉ የተከለከሉና ሲመለሱ የሞቱ አይሁዳውያንን ታሪክ ያስታውሳል…> አክቲቪስት ኦባንግ ሜቶ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ስደተናን ከሰባት የሙስሊም ሀገራት እንዳይገቡ የከለከለበትን እርምጃና እተካሄደ ያለውን ተቃውሞ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ ( ያድምጡት) <…የአሜሪካ ሕዝብ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ዘረኛ አይደለም አንዳንድ የእሱን ሀሳብ የሚደግፉ ስደተና የሚተሉ ሊኖሩ ቢችሉም በዚህ ሁለት ቀን ሙስሉሞች ብቻ ሳይሆኑ ዘረኛውን የትራምፕ ውሳኔ በርካታ አሜሪካውያን በኤርፖርቶች በዋይት ሐውስ በአጠቃላይ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተቃወሙ ነው ። ይሄ ብርታት ይሰታል ትራምፕ ብቻ የፈለገውን ማድረግ የሚችልበት አገር አይደለም የሕግ ስርኣቱ ጠንካራ ሕጋዊ ተቋሟቱ ይሰራሉ። ኢትዮጵአውአን በያለንበት ድምጻችንን ማሰማት ይህን መሰሉን ዘረና ድርጊት መቃወም አለብን ይሄ ለሙስሊም ብቻ የወጣ አይደለም ስደተናን ከመጥላት የመነጨ ውሳኔ ጭምር ነው። በግሪን ካርድ የያዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር ኤርፖርት ውስጥ ተይዘው እንደነበር ሰምተናል ይሄ መሰሉ እርምጃን ግን …> ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳዲቅ አህመድ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ከሰባት አገራት የመጡ ስደተኛ የሚያግደውን እርምጃ በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት) 1